መንግስት መታገስ እንጂ መልፈስፈስ የለበትም!

(ከመለስ አንደበት) “ዜጎች ሃሳባቸውን በሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ የመግለጽ መብት ተከብሮ ህግን አክብረውና አስከብረው በመብታቻው እንዲጠቀሙ ማድረግ ለጤነኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ወሳኝ የመሆኑን ያክል ቅሬታ አለኝ ያለ ሁሉ በጉልበትና በማስገደድ መፍትሄ የሚሻበት አማራጭ ከተፈቀደ የሚገነባው ስርዓትና ባህል የዴሞክራሲ ስርዓት መሆኑ ቀርቶ የብጥብጥ፤ የጉልበትና የጋጠወጥነት ስርዓትና ባህል እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።

በመሆኑም የህግ የበላይነትን በማስከበር ጉዳይ ላይ ጠንካራና የማያወላውል አቋም በመውሰድ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ ከፍተኛ ተጽዕኖ በመቋቋም፣ ስኳሁን የተገኘውን የልማት ድል ለማረጋገጥና ሰላም ለመጠበቅና አገሪቱን ለመበታተንና ህዝቦችን ለማናቆር በተለያዩ አካላት አጋፈሪነት የተሸረበውን ሴራ ለመቆጣጠርና የበሰለውን ዴሞክራሲ ባህል ሊጎለብት የሚችልበት ሁኔታ ለመፍጠር ምን ጊዜም መረባረብ ይገባል። ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን አገሪቷንና ህዝቦቿን አደጋ ውስጥ መውደቃቸው የማይቀር ነው።”