"ኒዮሊበራሊዝም ሞቶ ተቀብሯል ተብሎ መገለፅ አለበት"

መቐለ 02 ግንቦት 2011 የኒዮሊበራሊዝም ርእዮተ ዓለም በዋናነት በአሜሪካ እና እንግሊዝ እተዘወረ ከ1970ቹ ጀምሮ በርካታ የዓለም ሀገራት ብቁጥጥር ስር አውሎ የነበረ አስተሳሰብ ነው። ነፃ ገበያ፤ በገበያ ለሚፈጠር ክፍተትም ገበያውን ይፍታው በማለት እጅ እና እግሩ አጣጥፎ የሚቀመጥ ስርዓት ነው። አሁን ላይ ርእዮተ ዓለሙ እየከሰመ ሰለመምጣቱ በርካቶች ይናገራሉ።

የዓለም የምጣኔ ሀብት የሎሬት ሽልማት አሸናፊው እና የኮሎምብያ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ስቲግሊትዝ በትንታንያቸው የኒዮሊበራሊዝም ስርአት ሞቶ የተቀበረ ነው ሲሉ ይገልፁታል።

የቀድመው የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ደግሞ DEAD ENDS NEW BEGINNIGS በሚለው ፅሑፋቸው ኒዮሊበራሊዝም የከሰረ እና የሞተ ነው ብለውት ነበር። ሴባስትያን ቦክስፕ የተባለ የምጣኔ ሀብት ሙሁር ደግሞ ኒዮሊበራሊዝም ያበቃለት ጉዳይ ነው ጊዜው የተሻለ አመራጭ የሚፈለግበት ወቅት ነው ይላሉ።

አንዳኣንድ የፖለቲካ ተንታኞች ደግሞ ኒዮሊበራሊዝም የፖለቲካም የኢኮኖማም ካንሰር ነው ይሉታል። የኒዮሊበራሊዝም ኪሳራ ቀላል ምሳሌ ለመውሰድ እ.አ.አ በ1970 የላቲን ኣሜሪካዋ ሀገር ቺሊ ኒዮሊበራሊዝም ርእዮተ ዓለም ተቀበለች።

ሁሉም የመንግስት የልማት ድርጅትን ወደ ግል አዛወረች። ይህን ካደረገች በአጭር ጊዜ ውስጥ ታድያ በሀገሪቱ የስራ አጥንት ችግር እጅጉን ጨመረ፣ የኑሮ ውድነትም ጣራ ነካ የመጠጥ ውሃ ተቋማትም ወደ ግል ተዛውረው ስለነበር የሀገሪቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች የውሃ ክፍያ መክፈል ባለመቻላቸው ውሃ ተከለከሉ። በዚህም ምክንያት በሀገሪቱ ግጭት አለመረጋጋት ተከሰተ በ10 ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በግጭት ምክንያት ህይወታቸው አለፈ።

የሀገሪቱ መንግስት የኒዮሊበራሊዝም አስተሳሰብን አሸቀንጥሮ በመጣል በተከተለው ልማታዊ ፖሊሲ አሁን ላይ በላቲን አሜሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ከሚያዝመዘግቡ ሀገራት ተርታ ተሰልፋለች። ቦሊቪያ እና ህንድም የዚሁ የኒዮሊበራሊዝም ገፈት ቀማሾች ነበሩ።

አሁን ላይ በርካታ ሀገራት ኒዮሊበራሊዝም አይንህ ለአፈር እያሉበት ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ግን ወደ ኒዮሊበራሊዝም አስተሳሰብ እየተራመደች ትመስላለች። የኒዮሊበራሊዝም ዋና መገለጫው PRIVATIZATION ነው፤ ሁሉም ነገር ለባለሁለቱ እና ለገበያው መስጠት ኢትዮጵያም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ እንደምትተገብር አስታውቃለች።

ላለፉት ዓመታት ከኒዮሊበራሊዝ በተቃራኒ የልማታዊ መንግስት ስርዓት የተከተሉ እነ ጃፓን፣ ደቡብ ኮርያ፣ ታይዋን፣ ሆንግኮንግ እና ሲንጋፖር የደረሱበት የእድገት ደረጃ የሚታወቅ ነው። ኢትዮጵያም ልማታዉ ዴሞክራስያዊ አስተሳሰብን በመከተል መላው ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ ያደረገ ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት ስታስመዝግብ እንደነበረች የሚታወስ ነው።

አሁን ላይ አንድአንድ የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት ሙሁራን የኢትዮጵያ መንግስት ስለምን ዓለም እየተፋው ያለውን ስርዓት መረጠ ሲሉ በሀተታ መልክ ያስተቀምጣሉ።

(በአንገሶም አብርሃ) Dimtsi Weyane አማርኛ